አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ራሱን አገለለ

59
አዲስ አበባ ህዳር 3/2011 አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ራሱን አገለለ። ባለፉት ሁለት ዓመታት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ሲመራ የቆየው ኃይሌ ገብረስላሴ በትናንትናው ዕለት በሱሉልታ በተካሄደው የሩጫ ውድድር በአትሌቶች በኩል ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር የሚታወቅ ነው። ይህንን ተከትሎ ኃይሌ ራሱን ከፕሬዝዳንትነት ማግለሉን አስታውቋል። እስከ ቀጣይ የምርጫ ወቅት ድረስ የፌዴሬሽኑ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ተክታ እንድትሰራ መወከሉንም ገልጿል። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። ዛሬ ያቀረበው የመልቀቂያ ጥያቄ የሚጸድቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድ ይሆናል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም