በኮንጎ በሂቦላ በሽታ ከ200 በላይ ሰዎች ሞቱ

57
ህዳር 2/2011 በቅርቡ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተቀሰቀሰ የሂቦላ በሽታ ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትሩ እንደገለፀው በተከሰተው የሂቦላ በሽታ ተጎጂ ከሆኑት ነዋሪዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት  በሀገሪቱ በስተሰሜን አካባቢ በምትገኘዋ ኪዩ ተብላ በምትጠራዋ ክልል በቤኒ ከተማ ውስጥ መሆኑን ነው የጠቀሰው፡፡ በዚህችው  ከተማ ከስምንት መቶ ሺህ በላይ ህዝብ እንደሚኖር ነው ባለስልጣናቱ ያስታወቁት፡፡ በዚሁ በሽታ ሳቢያ 25 ሺህ ለሚደርሱ ነዋሪዎች ክትባት የተሠጠ መሆኑንም  ጨምረው የገለጸዋል፡፡ ይሁንና የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ኦሊ ኢላና ህክምናውን በተገቢው መንገድ ለማከናወን በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታቁ ሀይላት ተግባር ስራውን አዳጋች ደረገው መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት ሳቢያ በአካባቢው ክትባት የማመላለሱ ስራ ተቋርጾ እንደነበርም ነው የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ያስታወቀው፡፡ በኮንጎ ለዓመታት የእርስ በርስጦርነትና  በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ከሚስተዋልባቸው የአፍሪካ ሀገሮች መካከል አንዷ እንደሆነች ነው ቢቢሲ በድረ-ገጹ ያስነበበው፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም