የወላይታ ዞን ምክር ቤት የዋናና ምክትል አፈ ጉባኤ ሹመትን አጸደቀ

749

ሶዶ ጥቅምት 30/2011 የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዛሬ በጀመረው 4ኛ ዙር 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የዋናና ምክትል አፈ ጉባኤ ሹመትን አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ወይዘሮ አበበች ኢራሾን የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤና ወይዘሮ ዝናሽ በየነን  ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ ነባር አመራሮት ወደ ከፍተኛ ትምህርተ ቤት መግባታቸውን ተከተሎ ሹመቱን መስጠቱንና አዲስ አመራሮቹ የለውጡን ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል ብቃት ያላቸው ስለመሆናቸው በወቅቱ ተገልጿል።

እስከ ነገ በሚቆየው ጉባኤም የምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 6ኛ የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን እንዲሁም የ2010 አፈጻጸም ሪፖርት ለውይይት ቀርቦ እንደሚጸድቅ ተመልክቷል።

በተመሳሳይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2010 ዕቅድ አፈጻጻም ሪፖርት ቀርቦ የሚጸድቅ ሲሆን የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት የሟማያ ምርጫም እንደሚካሄድ ታውቋል ።

የወላይታ ብሔር የክልል እንሁን ጥያቄ ለምክር ቤቱ እንደሚቀርብና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶች እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡