ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎችአመራርና አባላትን ምደባ መርምሮ አጸደቀ

174
አዲስ አበባ ጥቅምት 30/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ የቋሚ ኮሚቴዎች አመራርና አባላት ምደባን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። ከዚህም ሌላ ምክር ቤቱ የአንድ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥራ ስንብትን የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረ በኋላ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ምክር ቤቱ ባለፈው ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ምደባን የውሳኔ ሀሳብ ሳያጸድቅ መቅረቱ የሚታወስ ነው። የአመራር ብቃት፣ የትምህርት ዝግጅት፣የስራ ልምድና የጾታ መመጣጠን በአመራር ምደባው ላይ ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት የህዝብ አንደራሴዎቹ በወቅቱ ገልጸዋል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገው ልዩ ስብሰባ ለቋሚ ኮሚቴ አመራርነት በቀረቡት 10 እጩዎች  ላይ አንድ በአንድ ድምጽ የሰጠ ሲሆን፤ አራት አመራሮችን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የሌሎች ተጨማሪ አራት አመራሮችን በአብላጫ ድምጽ ያጸደቀው ምክር ቤቱ፤ የቀሪ ሁለት አመራሮችን ሹመት ግን ውድቅ አድርጓል። በተያያዘ ዜና የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ "የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አየለ ዲቦ ከባድ የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽመው አግኝቻቸዋለሁ" ሲል በዳኛው ላይ  የስራ ስንብት ውሳኔ እንዲተለፍለት ለምክር ቤቱ  አቅርቧል። ስልጣንና ክብርን በመጠቀም ፍትህን ማዛባት ደግሞ ጉባኤው በዳኛው ላይ ያቀረበው ዋነኛ የዲሲፕሊን ግድፈት ነው። ምክር ቤቱም  የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች የድምጽ አሰጣጥ ዝርዝር፡- 1.የተከበሩ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ - የሴቶች ና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ - በሙሉ ድምጽ የጸደቀ፤ 2. .የተከበሩ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን-  ህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ- በ24 ተቃውሞ በ11 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ የጸደቀ፤ 3.የተከበሩ አቶ መሐመድ የሱፍ -  የመንግስት ወጪ አስተዳደርርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ-በሙሉ ድምጽ የጸደቀ፤ 4.የተከበሩ ወ/ሮ እምዬ ቢተው -  የሠው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ- በሙሉ ድምጽ የጸደቀ፤ 5.የተከበሩ አቶ ጌታቸው መለስ - የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ-በ1 ድምጸ ተዓቅቦ - በአብላጫ ድምጽ የጸደቀ፤ 6.የተከበሩ ወ/ሮ አልማዝ መሰለ - ግብርናና አርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ- በሙሉ ድምጽ የጸደቀ፤ 7.የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲያ የሱፍ -  የተፈጥሮ ሀብት መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ- በ6 ድምጸ ታዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀ፤ 8.የተከበሩ አቶ አሸናፊ ጋዕሚ -  የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳች ቋሚ ኮሚቴ- በ2 ድምፀጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀ፤ 9. የተከበሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ -  የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ-  በ109 ድጋፍ       በ152      ተቃውሞ በ33 ተዓቅቦ ያልጸደቀ፤ 10. የተከበሩ አቶ አፅብሃ አረጋዊ -  ለገቢዎችና ፋይናንስ ጉደዮች ቋሚ ኮሚቴ - በ102 ድጋፍ በ157 ተቃውሞ በ25 ተዓቅቦ ያልጸደቀ፤ ---END---  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም