የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን በመጪው ቅዳሜ ያካሂዳል - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን በመጪው ቅዳሜ ያካሂዳል

ጋምቤላ ጥቅምት 29/2011 የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በመጪው ቅዳሜ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስታወቁ። አፈጉ ባኤው አቶ ላክደር ላክባክ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት አስቸኳይ ጉባኤው የሚካሄደው የክልሉን መንግስት የሚመራው ጋህዴን በቅርቡ ባካሄደው ግምገማ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው። ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች ያቀረቡት የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አፈ ጉባኤው ገልጸዋል። በምትካቸውም አዲስ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንደሚሾሙ ይጠበቃል ።