የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ14 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የሰዓትና የቦታ ማስተካካያ አደረገ

97
አዲስ አበባ ግንቦት 14/2010 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ14 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የሰዓትና የቦታ ማስተካካያ ማድረጉን አስታወቀ። የፌዴሬሽኑ የሊግ ኮሚቴ በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ የሰዓትና የቦታ ማስተካካያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ማስተካካያ እንደተደረገ ገልጿል። በዚህም መሰረት ነገ በ23ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም 8 ሰአት የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስና የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ 9 ሰአት እንዲሁም 10 ሰአት የነበረው የደደቢትና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ 11 ሰአት ላይ ይካሄዳል። በ24ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰአት መከላከያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 10 ሰአት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰሀት ላይ ይካሄዳል። በ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልዲያ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከቀኑ 8 ሰአት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰአት ደደቢት ከአርባምንጭ ከተማ  ከቀኑ 10 ሰአት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰሀት ላይ ሆኗል። በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መሰረት ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዲያ ከተማ ከቀኑ 8 ሰአት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰአት መከላከያ ከጅማ አባጅፋር ከቀኑ 10 ሰአት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰዓት ተደርጓል። በተጨማሪም በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሃዋሳ ከተማ  ከቀኑ 8 ሰአት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰአት ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 11 ላይ የሚካሄድ ይሆናል። በ27ኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ወልዲያ ከተማ በሜዳው ከጅማ አባጅፋር ከቀኑ 8 ሰአት ላይ መካሄድ የነበረበት ጨዋታ ወልዲያ በስታዲየሙ ጨዋታ እንዳያደርግ የተጣለበት ቅጣት ባለመጠናቀቁ ምክንያት ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ይጫወታሉ። በተጨማሪም በ27ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም ደደቢትና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰሀት ላይ ይካሄዳል። በ28ኛ ሳምንት ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ ከወልዲያ ከተማ  ከቀኑ 8 ሰአት የነበረው ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰአት ኢትዮጵያ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት የሚያደርጉት ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰሀት ላይ ይከናወናል። የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮ ከታዩ ዋነኛ ሁነቶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የመርሃ ግብሮች መቋራረጥና መራዘም ይጠቀሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም