ኢትዮጵያና ስሎቫኒያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ

70
አዲስ አበባ ጥቀምት 5/2011 ኢትዮጵያና ስሎቫኒያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ። ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙትን የስሎቫኒያ ፕሬዝዳንት ባሮት ባሆርን በብሄራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች ላይ በጋራ መክረዋል። ፕሬዝዳንት ባሮት ባሆር ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ገለጻ፤ በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ጉብኝት "በስሎቫኒያና አፍሪካ ግንኙነት አዲስ ታሪክ የከፈተ ነው"። ከፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር በነበራቸው ውይይትም ሁለቱ አገራት በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በጋራ ለመስራት እንደተስማሙ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በበኩላቸው ስሎቫኒያ በንብ ማነብና በግብርናው ዘርፍ ካላት ስኬት ኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም እንደምትሻ አውስተዋል። ስሎቫኒያ የቀድሞ ዩጎዝላቪያ አካል የነበረች ስትሆን፤ የፕሬዝዳንት ባሮት ባሆር የኢትዮጵያ ጉብኝት ስሎቫኒያ እንደአገር ከተመሰረተመች በኋላ በአገር መሪ ደረጃ ከሰሃራ በታች የተደረገ የመጀመሪያው ጉብኝት ነው ተብሎለታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም