የንግድ ምልክት መብት ጥሰትን ለመከላከል የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

4417

ጅማ ጥቅምት 4/2011 የንግድ ምልክት መብት ጥሰትን ለመከላከል የንግድ ማህበረሰብና የፈጠራ ባለሙያዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንበረት የጅማ ቅርጫፍ ጽህፍት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ማሩ ዘውዴ ለኢዜአ እንደገለጹት የንግድ ምልክቶችንና የፈጠራ ስራዎችን  ማስመዝገብ  በማምረት፣ በማከፋፈልና በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ አካላትን መልካም ስምና ዝና ለመጠበቅና የመብት ጥሰትን ለመከላከል ያግዛል፡፡

መልካም ስምና ዝናን ከመጠበቅ ባለፈ በተመሳሳይ ምርቶችና አገልግሎቶች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የንግድ ምልክት መብት ጥሰት ለመከላከልና ሸማቾች የሚፈሉጉትን ምርትና አገልግሎት ለመለየት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የኮፒራይት መበት ጥስትን ለመከላከል የሙዚቃ፣ የስዕል ባለሙያዎች፣ የፍልም፣ ረጅምና የአጭር ልቦልድ ጸሃፊያን እና ሌሎችም የከነጥበብም ሆኑ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር የሚያያዙ የፈጠራ ስራዎች ባለቤትነትን ለማረጋገጥ  ማስመዘገብ ጠቃሚ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይም የአዕምሮ ንብረት መብቶች እንደማንኛውም ቁሳዊ ሃብት ሁሉ መጠበቅና ህጋዊ ዕውቅና ማግኘት አሰፈላጊ መሆኑን ህበረተሰቡ አውቆ  ወደ አዕምራዊ ንብረት ጽህፈት ቤት በመምጣት እንዲያስመዘግቡ ጠይቀዋል፡፡

በጅማ ቅርጫፍ ጽህፍት ቤት የከፍተኛ ፓተንት ባለሙያ አቶ ነጋ ወርቁ በበኩላቸው ”የአዕምራዊ  ንብረት በማስመዝገብ በኩል የህብተሰቡን ግንዛቤ የሚያሳደግ ስራ መስራት ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡

በመልካ ምድራዊ አቀማመጥ ምክንያት ልዩ ባህሪ ያላቸው የግብርና ምርቶችን በቅርብ ጊዜ በልዩ ትኩረት ለማስመዝግብ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

ለአብነትም በቅርቡ ከወለጋ ባህላዊ ምግብ መካከል አንጮቴ፣ ከጅማ ዞን የሊሙ ቡናና መሰል ምርቶችን እንዲመዘገቡ እየተሰራ ነው፡፡

በተጨማሪም ጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽህፍት ቤት ባርጩማን በወል ንግድ ምልክት ለማስመዘገብ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን እንደ እርኮቦትያሉና ሌሎች የጅማና አከባቢው ማህበረሰብ የሚታወቅባቸው ምርቶች እንዲመዘገቡ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በሊሙ  ኮሳ ወረዳ በሊሙ ገነት ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ መሃመድ ሚፍታህ እንደገለጹት የተቆላ ቡና መፍጫ፣ የጉድጓድ ውሃ መቆፈሪያና ሌሎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን በማስመዘገብ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

” የፈጠራ ስራዎቼን መስራት ከጀመርኩ የቆየሁ ቢሆንም ለማስመዝገብ የሚያግዝ ግንዛቤ ግን ከዚህ በፊት አልነበረኝም ” ብለዋል፡፡

በቅርቡ የጅማ አምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ባለሙያ በሰጣቸው ምክርና መረጃ መሰረት የተወሰኑ የፈጠራ ስራዎችን ለማስመዝገብ የተዘጋጁ መሆኑንም  ግልጸዋል፡፡