የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ይፋ ሆነ

83
ጥቅምት 3/2010 የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የመግቢያ ቀን ይፋ አደረገ፡፡ ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም የቅበላ ጊዜው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙንና የመቀበያ ጊዜውን ወደፊት እንደሚያሳውቅ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም በየተቋማቱ የተመደቡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች በመገኘት እንዲመዘገቡና ትምህርት እንዲጀምሩ አሳስቧል፡፡ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ተቋማት ሲሄዱም ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅና የስፖርት ትጥቅ አሟልተው እንዲጓዙም ጠቁሟል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ቀንም እንደሚከተለው ቀርቧል::
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም