ቻይና የጨረቃን ጠረፋማ ክፍል ለመቃኘት ሳተላይት ላከች

3586

ግንቦት 13/2010 ቻይና በጨረቃ ጠረፋማ(ጨለማ አካባቢ) ያለውን መልክዓ ጨረቃ በዚህ ዓመት ለማረጋገጥ በያዘችው እቅድ መሰረት የኮሚዩኒኬሽን ሳተላይት አምጥቃለች።

የቻይና ብሄራዊ የህዋ አስተዳደር ሳተላይቷ ዛሬ ማለዳ ወደ ህዋ መላኳን አረጋግጧል።

ሎንግ ማርች-4ሲ የተባለችው ሮኬት የተወነጨፈችው የቅኝት ሳተላይቷ በቻንግኤ 4 የጠፈር ተልዕኮ እና መሬት ላይ ባሉ ተቆጣጣሪዎች መካከል ተግባቦት መፍጠር የሚያስችል መሳሪያም ተገጥሞላታል።

ቻይና የአሁኑ ተልዕኮዋ ከመሬት በከፍተኛ ርቀት የሚገኘውን የጨረቃን የጠረፋማና ጨለማ ክፍል ለማወቅ ሳተላይቷን ወደ ጠፈር የላከች የመጀመሪያዋ ሀገር ያደርጋታል ነው የተባለው።

ሀገሪቱ በ2030 በጠፈር ምርምር አቅም ከአሜሪካ እና ከሩሲያ ጋር እኩል ለመሰለፍ ትልቅ ግብ ይዛ እየሰራች ነው።

ምንጭ፦ ዋሽንግተን ፖስት እና ሬውተርስ