የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አምቼ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካን ጎበኙ

664

አዲስ አበባ ጥቅምት 2/2011 የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ  በአዲስ አበባ የሚገኘውንና አምቼ በሚል የሚታወቀውን የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ጎበኙ።

አምቼ ‘ሲኤንኤች’ ተብሎ በሚጠራው የጣሊያን ተሽከርካሪ አምራችና በኢትዮጵያ መንግስት ሽርክና ከዛሬ 40 ዓመት በፊት የተቋቋመ ኩባንያ ነው።

አምቼ የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ በመገጣጠም ካለፉት አራት አስርት ዓመታት ጀምሮ ለአገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ትናንት ነው።