በቡራዩ የመልካ አቴቴ በዓል እየተከበረ ነው

91
አዲስአበባ መስከረም 27/2011 በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ አካባቢ የመልካ አቴቴ ኢሬቻ በዓል በመከበር ላይ ነው። የቡራዩው መልካ አቴቴ በዓል በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ቀጥሎ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው። ለዘመናት የኖረውን ባህላዊ እሴት ጠብቆ እየተከበረ ባለው የዘንድሮው የመልካ አቴቴ በዓልን አባ ገዳዎችንና የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ታድሞታል። የመልካ አቴቴ በዓል ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚሰባሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት፣ ሰላምና ፍቅር የሚማፀኑበት ክብረ በዓል ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም