በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ቻይና ድጋፍ ታደርጋለች-በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 20/2015 በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ቻይና ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ገለጹ።

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ላይ ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደሩ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ላይ ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ላይ ቻይና እንደምትደግፍ አምባሳደሩ በውይይታቸው አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ የሚያችል ስራ እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም