ዓለም አቀፍ አጋሮች የመልሶ ማቋቋም እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን እንዲደግፉ ጥሪ ቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፍ አጋሮች የመልሶ ማቋቋም እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን እንዲደግፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 17/2015 ዓለም አቀፍ አጋሮች የመልሶ ማቋቋም እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን እንዲደግፉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።
አቶ ደመቀ ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶቢያስ ቢልስትሮም ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ስዊድንን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች የመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ጥረቶችን ድጋፍ የማድረግ አስፈላጊነትም አንስተዋል።
የስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶቢያስ ቢልስትሮም በበኩላቸው የሰላም ስምምነት ሂደቱን አድንቀው ስምምነቱን ለመደገፍ አገራቸው ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
በውይይቱ ሁለቱ አገራት ያላቸውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የትብብር አድማሳቸውን ለማስፋት መስራት እንደሚገባ መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።