የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

የካቲት 16/2015 (ኢዜአ) ፦የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል።

የክልሉ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም