በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህርዳር ከተማ ይገናኛሉ

60
አዲስ አበባ መስከረም 25/2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 እግር ኳስ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከባህርዳር ከተማ አገናኝቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2010 ዓ.ም የአፈጻጻም ግምገማና የ2011 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት አካሂዷል። በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ሳምንት የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባህርዳር ከነማን ያስተናግዳል። ኢትዮጵያ ቡና በዚህ ዓመት ፕሪሚየር ሊጉን ከተቀላቀለው ከደቡብ ፖሊስ ጋር የሚጫወት ይሆናል። አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር ሲጫወት፣ ሽሬ እንዳስላሴ ከወላይታ ዲቻ፣ ሀዋሳ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ሲዳማ ቡና ደግሞ  በሜዳው ፋሲል ከተማን ያስተናግዳል። እንዲሁም መቀሌ ከተማ ከደደቢት፣ ደቡብ ፖሊስ ከመከላከያ ጋር የሚጋጠሙ ይሆናል። የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ከፋሲል ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት፣ ድሬድዋ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ፣ ወላይታ ዲቻ ከጅማ አባጃፋር፣ ሽሬ እንዳስላሴ ከሲዳማ ቡና ጋር ይገናኛሉ። እንዲሁም አዳማ ከተማ ከባህርዳ ከተማ፣ መቀሌ ከተማ ከደቡብ ፖሊስ፣ መከላከያ ደግሞ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ይጫወታሉ።                  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም