ኢትዮጵያ በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ እና የነፍስ አድን ቡድን ላከች

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 11/2015 ኢትዮጵያ በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ እና የነፍስ አድን ቡድን ላከች፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው ዕለት ከተርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን በስልክ ባደረጉት ቆይታ በተርኪዬ በደረሰው አደጋ ጥልቅ ሃዘን የተሰማቸው መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።

በዚህም ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጅዋን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት ትናንት አመሻሽ ላይ ኢትዮጵያ ወደ ተርኪዬ የቁሳቁስ ድጋፍ እና የነፍስ አድን ቡድን ልካለች።

ለቁሳቁስ ድጋፉና ለነፍስ አድን ቡድኑ ሽኝት ሲደረግም በኢትዮጵያ የተርኪዬ አምባሳደር ያፕራክ አልፕን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም