የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና ኢጋድ በትራንስፖርት መስክ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 6/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) በትራንስፖርት ዘርፍ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በኢጋድ ዋና መቀመጫ ጅቡቲ መከናወኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።

የትራንስፖርቱ ዘርፍ ከቀጠናዊ ትስስር ቁልፍ ሀሳቦች አንዱ መሆኑንና ስምምነቱ ይህን ራዕይ እውን ለማድረግ ወሳኝ አበርክቶ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም