ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላ ጋር ተወያዩ

160

ጥር 30/2015(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማልታው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላ ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች ዙርያ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጸቸው ባስተላለፉት መረጃ "የማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር እና መንግሥታቸው ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ" ብለዋል።

ሁለቱ ሀገሮች በተለያዩ ዘርፎች እርስ በርሳቸው የሚማሩት ብዙ ነገር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዛሬው ውይይት የተለያዩ የትብብር መስኮችን ይበልጥ አጠናክሯል ሲሉም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም