ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክዬ እና ሶርያ በተከሰተው ርዕደ መሬት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

407

አዲስ አበባ፣ ጥር 30/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡባዊ ቱርክዬ እና በሰሜን ሶርያ በተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ የሰው ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት የሀዘን መልዕክት "በደረሠው የሰው ህይወት ማለፍና ጉዳት አዝኛለሁ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ለተጎዱት ብርታትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም