ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 29/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር በሁለቱ ሀገራት ሁለገብ ግንኙነት እና ትብብር ላይ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት "ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር በሁለቱ ሀገራት ሁለገብ ግንኙነት እና ትብብር ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል" ብለዋል።

180 ሚልዮን ዩሮ እርዳታ እና ለስላሳ ብድርን የሚያካትት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መፈረም ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የዐሥር ዓመት የልማት ዕቅዳችንን ለማስቀጠል የሚደግፍ ነው ብለዋል።