ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአዲሱ የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

245

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 29/2015 የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአዲሱ የዓለም አቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡባካር ካምፖ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሳፈሩት መልዕክት ተቋማቱ በትብብር በሚያከናውኗቸው የህጻናት ጤና፣ስርዓተ-ምግብ እና የአስቸኳይ ግዜ ምላሽን በተመለከተ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዩኒሴፍ ለሚያደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ ከድርጅቱ ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር ሚኒስቴሩ ያለውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም