የሸገር ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

132

ጥር 27 ቀን 2015 (ኢዜአ) የሸገር ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ በሸገር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተዋናዮች ተገኝተዋል።

መድረኩ በከተማው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በሸገር ከተማ ከ4 ሺህ በላይ ኢንዱስትሪዎች ቢኖሩም ሥራ የጀመሩት ከ2 ሺህ እንደማይበልጡ የተገለጸ ሲሆን፤ ሥራ ያልጀመሩትን ወደ ተግባር ለማስገባት ንቅናቄው እንደሚያግዝ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም