ሴቶች የማህጸን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ ጤንነታቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል-ዶክተር ሊያ ታደሰ

103

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 24/2015 ሴቶች የማህጸን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ ጤናቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳሰቡ።

የማህጸን በር ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር አስመልክቶ ዶክተረ ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የካንሰር በሽታው አስቀድሞ ከታወቀ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መታከም እንደሚችል ገልጸዋል።

በተለይም እድሜያቸው ከ30 እስከ 49 ዓመት የሆኑ ሴቶች በሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች የሚሰጠውን የማህጸን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ አገልግሎት በማግኘት ጤናቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም