ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ቡድንን ሰብስበው ማነጋገራቸውን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ቡድንን ሰብስበው ማነጋገራቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 23/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ቡድንን ሰብስበው ማነጋገራቸውን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ዛሬ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ቡድን ሰብስቤ አነጋግሬያለሁ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያሉ ግብአቶችን የማምጣት እና ለትግበራ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን የማመንጨት ሥራ እንዲሠሩ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ” ሲሉም ገልጸዋል።