በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባቷን ነው--ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

363

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 20/2015፦ በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባቷን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

በውጊያ ልምምዱ አየር ሀይል ፣ ከባድ መሳሪያ ፣ልዩ ሀይል እና እግረኛ ተቀናጅቶ ውጊያን በአጭር የሚያስቀርባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ብለዋል።

በየቀኑ አይናችንን ከምንፈልገው ህልም እና ተግባራችን እንድናነሳ የሚሹ ሀይሎች ስላሉ የጦር መኮንኖች ዋና ተግባር የሚሆነው ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባት ነው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም