ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሦስትዮሽ መፍትሔ አፈላላጊ ቡድን አባላት ጋር ተወያዩ

ጥር 18/2015/ ኢዜአ/ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ቆይታቸው በፖለቲካው ሂደት ላይ ከተሠማሩ የተለያዩ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሦስትዮሽ መፍትሔ አፈላላጊ ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ውይይት፣ የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብ ያልሆነ መርሕ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር የሚሠራ መሆኑን ማረጋገጣቸው ተመላክቷል።

የሱዳን ሕዝብ እና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን እንዲፈልጉም ማበረታታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም