የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጥር 15 / 2015 (ኢዜአ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዴንማርክ የልማት ትብብርና አለም አቀፍ የአየር ንብረት ሚኒስትር ዳን ጆርገንሰን ጋር በሁለቱ ሀገራት የኢከኖሚ ትብብርና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅት ሚኒስትሩ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ስላሉ ሁለንተናዊ የልማት እንቅሰቃሴዎች፣ በመልሶ ማቋቋሙ ስለተከናወኑ ተግባራትና ስለሁለተኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዴንማርክ የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት አጋር መሆኗን አመልክተው ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የልማትና ሰብአዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ዳን ጆርገንሰን በበኩላቸው በቅርቡ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
ዴንማርክ ለኢትዮጵያ በልማት መስክ፣ በመልሶ ማቋቋምና በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ረገድ አስፈላጊውን እገዛ እንደምታደርግ አመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም የዴንማርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸውም መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡