በዛሬው እለት በይፋ የተጀመረው ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ታላቅ አደባባይና ፕሮጀክት ዋና ዋና ይዘቶች - ኢዜአ አማርኛ
በዛሬው እለት በይፋ የተጀመረው ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ታላቅ አደባባይና ፕሮጀክት ዋና ዋና ይዘቶች

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 9/2015 በዛሬው እለት በይፋ የተጀመረው ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ታላቅ አደባባይ ፕሮጀክት ዋና ዋና ይዘቶች;-
ፕሮጀክቶች በመሃል ከተማ ብቻ ሳይሆን በዳር አካባቢዎችም ማዳረስን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን
ግንባታው በ1.3 ቢሊዮን ብር በጀት የሚገነባ ነው፡፡
ከአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር ታሳቢ በማድረግ በአለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖች በማስተናገድ ለአካባቢው ተያያዠነት ያለው ጠቀሜታ እንዲኖረው ታስቦ የተገነባ ማዕከል ሲሆን አካባቢውንም በማስዋብ ከመንገድ አካፋዮች፤ አደባባዮችንና የእግረኛ መንገዶች ጋር ተናቦ የሚሰራ ሁለንተናዊ ፕሮጀክት ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት (PPP) ከጥበብ ዲዛይንና ቢዪልዲንግ ፒ.ኤል .ሲ ጋር በመተባበር በ10 ወራት ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ይህ ፕሮጀክት የስብሰባ አዳራሽ፤ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space) ፤ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ (gym )፤ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መናፈሻ፤ የመኪና ማቆሚያ ፤ሱፐርማርኬት፤ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች ፤የማንበቢያ ስፍራ፤ የመሳሰሉት ይኖሩታል፡፡
ፕሮጀክቱ 14ሺህ 400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፍ ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት በግንባታው ወቅት እስከ 1100 ያህል ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን በቀጣይ በቋሚነት ለ400 ዜጎቻችን የስራ ቦታቸው የሚሆን መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡