የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሺመልስ አብዲሳ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሺመልስ አብዲሳ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

ጥር 8/2015 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

በውይይት ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወታደራዊ መኮንኖች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በተከሰተው የፀጥታ ችግር የሰዎች መፈናቀል፣ የንብረት ዘረፋ እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች ማጋጠሙን የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

መንግስት የፀጥታ ችግሮችን በመፍታት የመሠረተ ልማት ችግሮችንና ሥራ አጥነትን ለመፍታት በትኩረት እንዲሰራ ተሳታፊዎቹ መጠየቃቸው ተመልክቷል።