የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የፋሲል ቤተ-መንግስትን ጎበኙ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 7/2015 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ የሚገኘውን የፋሲል ቤተ-መንግስትን ጎበኙ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን መሪዎችና ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ መሪነት ነው በጎንደር ከተማ የሚገኘውን የፋሲል ቤተ-መንግስትን የጎበኙት።

የሥራ ኃላፊዎቹ በጥዋቱ መርሀ-ግብር የጎርጎራ ፕሮጀክትን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም