ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾሙ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 3 /2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን ከጥር 02 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሹመዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ቀደም ሲል በኳታር እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም