ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 2/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቻይናን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደኅና መጡ ብለዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ "የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል ፤የዛሬው ውይይታችን ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል" ሲሉ ገልጸዋል።

አዲሱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ነው አዲስ አበባ የገቡት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም