የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 1/2015 የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር ፋርዶዋስ ኦስማን ኤጋል ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
በሚኒስትሯ የሚመራው ልዑክ ቡድን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አቀባበል አድርገውለታል፡፡
በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሲቪል አቪየሽን መስክ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡