ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሮጀክቶች ስራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሠራተኞች ማዕድ አጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሮጀክቶች ስራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሠራተኞች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 30/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው በሚመሩ የልማት ፕሮጀክቶች እየተሳተፉ ለሚገኙ ሠራተኞች ማዕድ አጋርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚመሩ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሠራተኞች ነው የበዓል ማዕድ ያጋሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትላንትናው እለትም በዓልን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ሁሉም ከፍለ ከተሞች ለተውጣጡ በድምሩ 150 ለሚሆኑ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎች የበዓል ማዕድ ማጋራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
