የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 29/2015 የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል(ገና) መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
“ደማቅ የሆነው የገና በዓል ለእምነቱ ተከታዮች የተትረፈረፈ ደስታ እና እርካታ አንዲያመጣላቸው እንመኛለን” ሲል በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል ምኞቱን ገልጿል።

በአዲስ አበባ የስዊድን ኤምባሲ “እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ” በሚል የመልካም ምኞቱን ገልጿል።

ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፖላንድ፣ ዩክሬን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኢንዶኔዢያ፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ስዊዘርላንድ እና ሞሮኮ ሌሎች የበዓል መልካም ምኞታቸውን የገለጹ አገራት ናቸው።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።