ማዕከሉ የኮማንዶ ሰልጣኞችን ዛሬ አስመረቀ

ብላቴ (ኢዜአ) ታህሳስ 29 ቀን 2015 በብላቴ የሚገኘው የኮማንዶ አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የኮማንዶ ሰልጣኞችን ዛሬ አስመረቀ።

በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

የኮማንዶ አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦችም በመርሀ ግብሩ ታድመዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች ቀደም ሲል ከተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች መደበኛ የእግረኛ ወታደራዊ ስልጠና በተሻለ ውጤት ተመርቀው በማዕከሉ የኮማንዶ ኮርስ እንዲወስዱ የተመረጡ መሆናቸው ታውቋል።

ማዕከሉ አሁን ላይ ዘመኑን የዋጀ ሰራዊት በመገንባት በመንግሥት የተያዘውን ውጥን ለማሳካት እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።

የዕለቱ ተመራቂ ኮማንዶዎቹ በተኩስ ወረዳ በተራራ መሰናክልና በጂምናዚየም ስፍራ ለክብር እንግዶቹ ወታደራዊ ትርሂት አሳይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም