አምባሳደሮች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የስፖርት ውድድር እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ ኢዜአ ታህሳስ 28/2015፦ በተለያዩ ሃገራት ኢትዮጵያን እያገለገሉ ያሉና አዳዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የስፖርት ውድድር እያካሄዱ ነው።

የስፖርት ውድድሩ ተሳታፊዎች በተለያዩ ሃገራት ከሚያገለግሉት አምባሳደሮች በተጨማሪ በዋናው መስሪያ ቤት የሚያገለግሉ እና አዳዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ናቸው።

በሱሉልታ ያያ ቪሌጅ ያዘጋጀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው።

"ባህላችን የዲፕሎማሲያችን መሰረት ነው" በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወነው የአምባሳደሮች የስፖርት ውድድር በመረብ ኳስ፣ በእግር ኳስ፣ በገና ጨዋታ፣ በጠረጴዛ ቴኒስና በገመድ ጉተታ የስፖርት አይነቶች የሚካሄደው ነው።

በውድድሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም