የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የቀድሞ ሊቀ ጳጳስ ኤሜራተስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 27/2015 የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የቀድሞ ሊቀ ጳጳስ ኤሜራተስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈጽሟል።

ጀርመናዊው ጳጳስ ባሳለፍነው ሳምንት በሚኖሩበት “ማተር ኢክሌሳኤ’ ገዳም በ95 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

ኤሜራተስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ቀብራቸው ዛሬ በቫቲካን ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን አሶሲዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የወቅቱ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የጀርመኑን ጳጳስ የቀብር ስነ ስርዓት መምራታቸው ተገልጿል።

ከቀብራቸው በፊት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው የአስክሬን ሽኝት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መገኘታቸውን የአሶሲዬትድ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል።

ቤኔዲክት 16ኛ እ.አ.አ 2013 ከጵጵስናቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው የሚታወስ ነው።

ኤሜራተስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ለዘጠኝ ዓመታት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም