ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ሕልም ያለውን ታዳጊ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ራዕዩን እንዲሳካ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 27/2015 የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ሕልም ያለውን ዳግማዊ ቴዎድሮስ ራዕ እንዲሳካ ድጋፍ እንደሚያደርጉለት ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቷ በ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ኢትዮጵያን ያስተዋወቁትን ቴዎድሮስ ባጫ እና ልጁን ዳግማዊ ቴዎድሮስን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከሕጻንነቱ ጀምሮ የኳስ ችሎታን ያዳበረ እና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ሕልም እንዳለውና ይሄንኑ ሕልሙን ለማሳካት አባቱ ቴዎድሮስ ባጫ ድጋፍ እያደረገለት እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በሩሲያ ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው 21ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንዲሁም በኳታር በቅርቡ በተካሄደው 22ኛው ዓለም ዋንጫ አባትና ልጅ በክብር እንግድነት በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ተጋብዘው መታደማቸው የሚታወስ ነው።

ዳግማዊ ኳስ በማንጠባጠብ የሁለት ብር ቻሌንጅ አስጀምሮ 974 ጊዜ ኳስ በማንጠበጠብ ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ገንዘብ ማሰባሰቡ ይታወቃል።

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዳግማዊ ቴዎድሮስ የእግር ኳስ ችሎታውን እንዲያዳብር ማበረታታቸውንና ራዕዩ እንዲሳካ ድጋፍ እንደሚያደርግለትም ገልጸዋል።

የእግር ኳስ አካዳሚው መግባት ዋነኛው አማራጭ በመሆኑ ሁሉም ሊደግፉው እንደሚገባ መናገራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም