ኢንዱስትሪን ማሳደግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ትልቅ ሚና አለው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
ኢንዱስትሪን ማሳደግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ትልቅ ሚና አለው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ታህሳስ 26/2015 (ኢዜአ) ኢንዱስትሪን ማሳደግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በገላን ከተማ የሚገኘውን ሆራ ኢንዱስትሪን መጎብኘታቸው ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ "ዛሬ በገላን ከተማ የኢትዮጵያ ታምርት ሁለተኛውን ጉብኝት ያደረግነው በሆራ ኢንዱስትሪ ነው" ብለዋል።

በዚህ ኢንዱስትሪ ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ ፣ መቁያ እና ሲሚንቶ ማሸጊያ ማምረቻ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢንዱስትሪን ማሳዳግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው ፤በድጋሜ በኢትዮጵያ ታምርት ተሳተፉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::