የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ የሚያደርገውን በረራ ዛሬ ዳግም ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ የሚያደርገውን በረራ ዛሬ ዳግም ጀመረ

ታህሳስ 24/2015(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሁለት ዓመታት ያህል አቋርጦት የነበረውን ከአዲስ አበባ ወደ ሽሬ የበረራ አገልግሎት ዛሬ ዳግም ጀምሯል።
ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ሽሬ በተጀመረው በረራ የተጓዙ መንገደኞች ለኢዜአ እንዳሉት፣ የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት በዘላቂነት ለማቆም የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሽሬ በረራ በመጀመሩ ደስታ እንድተሰማቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ የበረራ አገልግሎት መጀመሩ መንግስት የሰላም ስምምነቱን እየተገበረ መሆኑን በተጨባጭ ማሳያ ነው ብለዋል።

"አሁን በተፈጠረው ነገር ደስ ብሎናል" ያሉት መንገደኞቹ፣ ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ ለተፈጠረው ሰላም ዘላቂነት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።