ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2023 አዲስ ዓመትን ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞታቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 23/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2023 አዲስ ዓመትን ለሚያከብሩ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በሙሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት አዲሱ ዓመት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት እንዲያመጣ እመኛለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም