የዓለም ዋንጫው የምንጊዜም ከፍተኛ የግብ አስቆጣሪዎች እነማን ናቸው?

281

አዲስ አበባ ታህሳስ 7/2015 (ኢዜአ) የፊፋ ዓለም ዋንጫ እ.አ.አ በ1930 በኡራጓይ ጅማሬውን አድርጎ ዛሬ በኳታር 22ኛው ውድድር ላይ ደርሷል።

አንድ የእግር ኳስ ተጫዋች በዓለም ዋንጫ ላይ ግብ ማስቆጠር ትልቁ ፈንጠዝያ እና ደስታው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

በተለያዩ ዓለም ዋንጫዎች ከደስታ ባለፈ ተጫዋቾች ግብ ሲያስቆጥሩ ስሜታቸውን በማልቀስ ሲገልጹም መመልከት ተችሏል።

በ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በምድብ ሶስት ፖላንድ ሳዑዲ አረቢያን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የፖላንዱ አምበል ሮበርት ሌዋንዶውስኪ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ግብ ሲያስቆጥር ስቅስቅ ብሎ በማልቀስ ደስታውን የገለጸበት መንገድ የእግር ኳስ ቤተሰቡን ቀልብ የሳበ ነበር።

በተለያዩ ዓለም ዋንጫዎች ከአንድ ጎል በዘለለ በተደጋጋሚ ጊዜ ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ የጻፉ ተጫዋቾች አሉ።

የ89 ዓመቱ ፈረንሳዊ አዛውንት ጀስት ሉዊስ ፎንቴን እ.አ.አ በ1958 ስዊድን ባሰናዳችው ስድስተኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በስድስት ጨዋታ 13 ግቦችን በማስቆጠር በአንድ ዓለም ዋንጫ ብዙ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ታሪክ ባለቤት ናቸው።

ጀስት ፎንቴን ግን የዓለም ዋንጫው የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ አይደሉም።

ለመሆኑ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች እነማን ናቸው?

በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪካቸው ከ10 እስከ 16 ጎል በማስቆጠር የተለዩ ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል ፦

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም