የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰባት አባላት ያሉት ጸረ ሙስና ኮሚቴ አቋቋመ

108

አሶሳ (ኢዜአ ታህሳስ 04/2015) ሙስናን በተደራጀ አግባብ በመከላከል የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የጸረ ሙስና ኮሚቴውን እንደሚያግዝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰባት አባላት ያሉት ጸረሙስና ኮሚቴ ዛሬ አቋቁሟል።

እየተስተዋለ ያለውን ብልሹ አሰራርና ሙስናን ለመከላከል አገር አቀፍ የጸረ ሙስና ኮሚቴ በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

ክልሎችም ይህንኑ ለማገዝ በሚያስችላቸው መልኩ የየራሳቸውን የጸረ ሙስና ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ እየገቡ ነው።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ሰባት አባላት ያሉት የጸረ ሙስና ኮሚቴ ዛሬ ተቋቁሟል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1ኛ. አቶ ሠይድ ባበክር፦ የኮሚቴው ሠብሳቢ

2ኛ. ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ፦ አባል

3ኛ. ምክትል ኮሚሽነር አምሳሉ ኢረና፦ አባል

4ኛ. አቶ ነጂ ኖኖ፦ አባል

5ኛ. አቶ ከማል ሀሰን፦ አባል

6ኛ. አቶ መሀመድ ሃሚድ አባል

7ኛ. አቶ ሙክታር አብዱላሂ የክልሉ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ አባላት ሆነው ተሰይመዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኮሚቴው የተቋቋመበት ዓላማ በክልሉ ሙስናን በተደራጀ አግባብ በመከላከል የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል እንደሆነ አመልከተዋል፡፡

ኮሚቴው ከዛሬ ጀምሮ ስራውን በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገልጸው ሁሉም የክልሉ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞችና መላው ህዝቡ ኮሚቴውን እንደሚያግዙ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም