17ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

441

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 25/2015 17ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ “ህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው።

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች የሚወክሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን እና ህዝቦች የባህል ምግቦች፣ አልባሳት እና ባህላዊ ውዝዋዜዎች እየቀረቡ ነው።

በፌስቲቫሉ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የመዲናዋ ነዋሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች ተገኝተዋል።

17ኛው የብሄር በሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የፊታችን ሀሙስ ህዳር 29 ቀን 2015 በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ መገለጹ ይተወሳል።