ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገለፁ

368

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 23/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ቢን ዛይድ እና ለሀገሪቱ ህዝቦች ብሔራዊ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትና መልካም ምኞታቸውን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ገፃቸው ባስተላላፉት መልዕክት ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንትና ለህዝቡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ለውድ ወንድሜና ጓደኛዬ ለፕሬዚዳንት ሞሐመድ ቢን ዛይድ እንዲሁም የተከበረው የተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ህዝብ እንኳን ለ51 ኛው ብሔራዊ ቀን አደረሳችሁ” ብለዋል።

በዛሬው ዕለት 51ኛ ብሔራዊ ቀን ሆኖ የሚከበረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ሕዝቦች በዓል እ.አ.አ 1971 ጀምሮ መከበር የጀመረ ሲሆን በአረብ ኤመሬት ውስጥ ለየብቻ ይተዳደሩ የነበሩ ኤሜሬቶች ወይም ግዛቶች በአንድነት መተዳደር የጀመሩበት ዕለት ነው።