ደኢህዴን 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

71
መስከረም 18/2011 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በሃዋሳ  ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ጉባኤው "የህዝቦች አንድነት ለሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መሪ ሃሳብ  የሚካሄድ ነው። በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤና የድርጅቱ ሊቀመንበር እና  የድርጅቱ ምክትል ሊቀመበርና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ጨምሮ  ከ1 ሺህ 200 በላይ አባላት ታድመዋል። በጉባኤው ላይ ከተሳተፉት ከ1 ሺህ 200 በላይ አባላት ውስጥ 800  በድምጽ  ቀሪዎቹ በታዛቢነት  የሚሳተፉ መሆናቸውን ታውቋል፡፡ የድርጅቱ አርማ እና ስያሜ ለውጥን በተመለከተም በጉባኤው ውይይት ተደርጎበት አቅጣጫ እንደሚቀመጥበት ይጠበቃል። በጉባኤው ወጣቱን ወደ አመራርነት ለማምጣት በተያዘው ድርጅታዊ አቅጣጫ መሰረት ከነባሮቹ የተወሰኑትን በክብር በማሰናበት በምትካቸው አዳዲስ ወጣት አመራሮች እንደሚመረጡም እንደዚሁ፡፡ የደኢህዴን ጉባኤው የክልሉን ህዝቦች በተለይ የወጣቱን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች ይወሳናሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም