የሰብአዊ ድጋፍ ወቅታዊ መረጃ

169

በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሃት መካከል በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ መንግስት ቃል የገባውን በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ለመድረስ መንግስት ከአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በሶስት አቅጣጫ (ኮሪደር) ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ እያጓጓዘ ይገኛል።

ያለፉት አራት ቀናት ዋና ዋና የሰብአዊ ድጋፍ መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፤
በጎንደር ኮሪደር
• ህዳር 17- ከጎንደር በሁመራ በኩል ወደ ሽሬ 1,137 ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል
የጫኑ 30 የአለም ምግብ ድርጅት የጭነት መኪኖች ተልከዋል፤ በተጨማሪም 212 ሜትሪክ ቶን እህል የጫኑ 10 የጭነት መኪኖች ከጎንደር ወደ ከማይፀብሪ ተጓጉዘዋል
• ህዳር 18- የአለም ምግብ ድርጅት በ24 መኪኖች 1,043 ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ከጎንደር ወደ ሽሬ ተልኳል
• ህዳር 19- ከሽሬ ወደ ማይፀብሪ የእርዳታ እህል የሚያጓጉዙ 11 ከባድ ተሽከርካሪዎች እየተጫኑ ነው
• ህዳር 20- 380 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ የጫኑ 17 የአለም ምግብ ድርጅት የጭነት መኪኖች ከጎንደር ወደ ማይ ፀብሪ ̸ዲማ ተልከዋል።

እንዲሁም ከጎንደር ወደ ሽሬ የምግብ ድጋፍ አድርሰው 9 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር ተመልሰዋል።
በኮምቦልቻ ኮሪደር
• ህዳር 17- ከኮምቦልቻ የተነሱ 626 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍን የጫኑ 22 የጭነት ተሽከርካሪዎች ዛታ ደርሰዋል
• ህዳር 18- የአለም ምግብ ድርጅት 54 የምግብ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኮምቦልቻ ተነስተው ወደ ኦፍላ፤ ራያ አላማጣ ደርሰዋል
• ህዳር 19- በደቡባዊ ዞን ውስጥ ለሚገኙት ባላ፤ ኮረምና ሌሎችም ወረዳዎች የሚላክ የምግብ እህል ጭነት እየተካሄደ ነው
በሰመራ ኮሪደር
• ህዳር 17- 34 የተለያየ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደርሰዋል።

መቀሌ የገቡት የድጋፍ አይነቶች፤ 77 ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች፣ 1,223 ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል እንዲሁም 95,272 ሊትር ነዳጅ ናቸው
• ህዳር 18- በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ በኩል የተላኩ በድምሩ 175 መኪኖች መቀሌ ደርሰዋል።
• ህዳር 20- የምግብ ድጋፍ የጫኑ 140 ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቀሌ ጉዞ ጀምረዋል ።
የበረራ አገልግሎት
• ህዳር 20- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ የአየር በረራ አገልግሎት በኩል ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የመንገደኞች የአውሮፕላን በረራ ተከናውኗል።

ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም