የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት የአክሱም ጽዮን ማርያም የንግስ በዓልን በድምቀት አክብረናል- የበአሉ ታዳሚዎች

205

ህዳር 21/2015(ኢዜአ) የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓልን በድምቀት ማክበር ችለናል ሲሉ በበዓሉ የተገኙ የእምነቱ ተከታዮች ገለጹ፡፡

በየዓመቱ ህዳር 21 ቀን የሚከበረው የጽዮን ማርያም በዓል ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

በክብረ በዓሉ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የእምነቱ ተከታዮች እንዳሉት፣ ባለፈው ዓመት በጸጥታ ስጋት ምክንያት በርካታ ምእመናን በዓሉን በስፍራው በመገኘት አለማክበራቸውን አስታውሰዋል፡፡

በዘንድሮ ዓመት ግን የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት ምክንያት በዓሉ ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሯል ብለዋል።

ዘንድሮ አከባበሩ ካለፈው ዓመት የተሻለ መሆኑን የገለጹት አስተያየት ሰጭዎቹ፤ በቀጣይም ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ከዚህ በበለጠ በድምቀት ለማክበር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም